የተቀናጀ የሥራ መረጃ አያያዝ ሥርዓት በሥራ ዕድል ፈጠራ መረጃ አያያዝ ላይ ግለሰባዊ ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍን ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከ11ዱም ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ 130 የወረዳና የክፍለ ከተማ የሥራ ስምሪት አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ማሻሻያ በተደረገለት የተቀናጀ የሥራ መረጃ አያያዝ ሥርዓት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል።
በሥልጠናው
መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው መመሪያ የሰጡት የቢሮው የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰባህዲን ሱልጣን ሥርዓቱ ላለፉት ስድስት ወራት ተግባራዊ ሲደረግ ቢቆይም አሠራሩን ይበልጥ ግልጽ ፈጣንና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ አዲስ ማሻሻያ መደረጉን ገልጸዋል።
ዳይሬክተሩ
ባለሙያዎቹን ሲያሳስቡ ቀደም ሲል የነበረው የጋራ ተጠቃሚ ስምና የይለፍ ቃል አጠቃቀም ለማንኛውም የመረጃ ግድፈት ተጠያቂ የሚያደርግ ባለመሆኑ የሥራ ዕድል ሳይፈጠር እንደተፈጠረ ተደርጎ መመዝገብንና የዕድሜ መረጃ መዛባትን ጨምሮ ለተለያዩ ብልሹ አሠራሮች በር ከፍቶ መቆየቱን ጠቁመዋል።
ይህንን
ክፍተት ለመሙላት ለእያንዳንዱ ባለሙያ የግል መለያ ስምና የይለፍ ቃል እንዲኖረው የተደረገ ሲሆን ይህም ማንኛውም ባለሙያ ወደ ሥርዓቱ የሚያስገባው መረጃ በራሱ መለያ ስለሚመዘገብ ለሚፈጠሩ ስህተቶች ቀጥተኛ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ነው።
የተቀናጀ
የሥራ መረጃ አያያዝ ሥርዓት በአካል ወደ መሬት ወርዶ መረጃዎችን ለማጣራት የሚባክነውን ጊዜና የሰው ኃይል ከመቀነሱም ባለፈ የሥራ ኃላፊዎች ያሉበት ቦታ ሆነው በሞባይል ስልካቸው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን በቀጥታ እንዲከታተሉና ፈጣን ውሳኔ እንዲሰጡ ዕድል ይፈጥራል።
ሥርዓቱ
ከነገ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን ባለሙያዎችም የተሰጣቸውን የግል መለያ በሚስጥር በመያዝ መረጃዎች እንዳይባክኑ በማድረግ ለዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲተጉና ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
<<ከፍታን ማፅናት፤
ነገን ማላቅ>>
No comments yet. Be the first to comment!