የሥራና ክህሎት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋዮችን እያረካ መሆኑ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የባለጉዳይ ቀንን አስመልክቶ በሰጠው አገልግሎት ተገልጋዮች ያለምንም እንግልትና መጉላላት ጉዳያቸውን ማከናወን መቻላቸውን ገለጹ።
የሥራና ክህሎት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋዮችን እያረካ መሆኑ ተገለጸ።
🇪🇹 ሚያዝያ 9/2018 ዓ.ም 🇪🇹
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የባለጉዳይ ቀንን አስመልክቶ በሰጠው አገልግሎት ተገልጋዮች ያለምንም እንግልትና መጉላላት ጉዳያቸውን ማከናወን መቻላቸውን ገለጹ።
ቢሮው በተለይም መረጃዎችን አስቀድሞ ግልጽ በሆነ መልኩ ለተገልጋዮች ተደራሽ ማድረጉ ለስራው መሳካት ትልቅ እገዛ ማድረጉ ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት ከኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማህበር የመጡት ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት ለሰራተኞቻቸው የቅጥር ውል ለመፈጸም የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችንና ፎርማቶችን ቢሮው አስቀድሞ በግልጽ እንዲያውቁ በማድረጉ ሰራተኞቻቸው ሳይጉላሉ ውላቸውን ፈርመው ወደ ስራ እንዲመለሱ አስችሏል።
ስራ አስኪያጁ አክለውም ይህ አሰራር ወደፊት በኦንላይን ቢታገዝ የባለጉዳዮችን ጊዜና ገንዘብ ይበልጥ መቆጠብ እንደሚቻል ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ ከሰፖርት ስትሪት ችልድረንስ ኤንድ ማዘርስ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የመጡት አቶ ተስፋለም አቅመ ደካማ ለሆኑ ዜጎች በእንጨት ስራ፣ በልብስ ስፌትና በጸጉር ሙያ ስልጠና ለመስጠት እንዲችሉ ሰልጣኞችን ለመመልመል ወደ ቢሮው በመጡበት ወቅት በደቂቃዎች ውስጥ አስፈላጊውን መረጃ በማግኘት ቀልጣፋ አገልግሎት እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ከየካ ክፍለ ከተማ የመጡት የብርሃኑ ሄኖክ ኮንስትራክሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ቢሮው እያከናወነ ያለውን የትስስር ስራ አድንቀው ጉዳያቸው በቅደም ተከተል መሰረት ምላሽ እንደሚያገኝ በኃላፊዎች በኩል የተሰጣቸው ምላሽ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቁመዋል።
አቶ ብርሃኑ አክለውም ይህ መሰሉ ድጋፍ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።
ከቤቶች ልማት በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ለደረጃ እድገት ጥያቄ የመጡት አቶ ንጋቱ ኃይሉ በበኩላቸው ምንም እንኳን የሚመለከታቸው አካል በወቅቱ ባለመገኘታቸው ለሌላ ቀን ቢቀጠሩም በቢሮው በኩል የተደረገላቸው አቀባበልና የተሰጣቸው ግልጽ መረጃ ጥሩ መሆኑን መስክረዋል።
በአጠቃላይ ከባለጉዳዮች የተገኘው አስተያየት እንደሚጠቁመው፣ ቢሮው ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት የዜጎችን ጥያቄዎች በወቅቱ ለመመለስ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
<<ፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@bols20116?_t=ZM-8y9L28EOubG&_r=1
https://www.facebook.com/addisababatvetbureau
👉Telegram
https://t.me/AABOLS
👉YouTube
https://youtube.com/@bureauoflaborandskill?si=t9ZklwKzGx9rRyXf
👉website
https://aabols.gov.et
👉ለቅሬታ፣ አስተያየትና ጥቆማ
https://complain.aabols.gov.et
👉ለነፃ የስልክ ጥሪ
6524
No comments yet. Be the first to comment!