ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሀ ግብር አገልግሎት አሰጣጥና ደንበኛ አያያዝ ዙሪያ ተካሄደ።
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት በሳምንቱ የመጀመሪ ቀን የሚካሄደውን የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በሚል መርህ በየሳምንቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መካሄዱን ቀጥሏል።
ወርቃማ ሰኞ
August 28, 2025
308 views
ነሐሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት በሳምንቱ የመጀመሪ ቀን የሚካሄደውን የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር <<ወርቃማ ሰኞ ለወርቃማ ሳምንት>> በሚል መርህ በየሳምንቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መካሄዱን ቀጥሏል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ትኩረቱን በአገልግሎት አሰጣጥና ደንበኛ አያያዝ ዙሪያ በቢሮው የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት አቶ እሸቱ ንጉስ አማካኝነት ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማሟላት በሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም አገልጋይ ባለሙያዎች ሊላበሷቸው ስለሚገባ የስነ-ምግባር መርሆዎች ተነስተዋል።
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ከማሟላት ባሻገር የተገልጋይ ባህሪያትን ቀድሞ በመረዳት ደንበኛን በአግባቡ መያዝ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>
No comments yet. Be the first to comment!