የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎቹን ኑሮ በዘላቂነት ለማሻሻል በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።
አቶ ሚሊዮን ማትዮስ፦ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
ስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና
Abdi Awol
April 20, 2026
34 views
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከአቅመ ደካሞች ጋር በዓል አክብሯል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ በመርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎቹን ኑሮ በዘላቂነት ለማሻሻል በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ጠቅሰው በዓሉን ምክኒያት በማድረግ በጋራ ማዕድ በመጋራታቸው ደስተኛ በሆናቸውን ገልፀው
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው ያለንን ተካፍለን በዓላትን በጋራ የማሳለፍ የቆየ እሴታችን ነው ብለው ይህንን ነባር እሴታችንን ይበልጥ ለማጠናከር የተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
No comments yet. Be the first to comment!